120K+ Population
4 Tourism Sites
7 Cultural Values
3 Languages
Our Story

About Jille

A region rich in history, natural resources, and vibrant communities.

ታሪካዊ ዳራ

ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የስም ስያሜዋን ያገኘችው የወረዳው ነዋሪዎች ከሆኑ ከአምስቱ ጅሌ እና ሱባ ጥሙጋ ሲሆን ጅሌም ሆነ ጥሙጋ በወረዳው ውስጥ የሚኖሩ የኦሮሞ አባቶች ስም እንደሆነ ከሽማግሌዎችና እድሜ ጠገብ አባቶች የተገኙ ታሪኮች ያወሳሉ፡፡ ይህ ወረዳ በዚህ ስያሜ መጠራት የጀመረው በደርግ ስርዓተ መንግስት የወረዳዎችና ዞኖች ምስረታ ወቅት እንደሆነና በሰሜን ሸዋ ክፍላ ሀገር ይፋትና ዱሙጋ አውራጃ ኤፍራታና ጅሌ ወረዳ በመባል እንደምትታወቅ የተለያዩ በጽሁፍ የሚገኙ ድርሳኖችና መጻጽፎች እንዲሁም አፈታሪኮች ያሰረዳሉ፡፡ ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ይህን አሁን የምትጠራበትን ስያሜ ራሷን ችላ ያገኘችው ከ1986 ዓ/ም መባቻ ላይ ከኤፍራታና ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ከተለየችበት ጊዜ አንስቶ ሲሆን የወረዳዋ ዋና ከተማ ሰንበቴ በማድረግ ተመሰረተች፡፡ በ1987 ዓ/ም የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ራሱን ችሎ በተመሰረተበት ወቅት ከአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጋር በመቀላቀል አርጡማ ጅሌ የሚል ስያሜ ተስጥቷት እስከ 1993 ዓ/ም መቆየቷም ይነገራል፡፡ የስሟ ስያሜ እንደየወቅቱና ነባራዊ ሁኔታ ሲቀያየር መጥቶ ከ1993 ዓ/ም መባቻ ላይ ከአርጡማ ጅሌ ወረዳ በመለየት ራሷን ችላ ዛሬ ለምትጠራበት ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ስያሜ ላይ ደርሳለች፡፡ እምነትና ቋንቋ በወረዳዋ ውስጥ ከሚኖረው ማህበረሰብ 99% የሚሆነው የእስልምና እምነት ተከታይ ሲሆን 1% የሚሆኑት የተለያየ እምነት ተከታይ እንደሆኑ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ከቋንቋ አንፃር 95% ኦሮሚኛ ተናጋሪ ሲሆኑ 5% አማርኛ ተናጋሪ ናቸው፡፡

አካባቢ እና ስነ-ህዝብ

በኢትዮጵያ እምብርት ላይ የሚገኝ፣ የተለያዩ ህዝቦች መኖሪያ።

ግብርና

ለም መሬቶች ጥራጥሬ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ያመርታሉ።

የእንስሳት እርባታ

የእንስሳት እርባታ ምግብ፣ ገቢ እና ወጎችን ያስቀጥላል።

ተፈጥሮአዊ ሀብቶች

በለም አፈር፣ በውሃ አካላት እና በብዝሃ ህይወት የታደለች።

ንግድ

ታዋቂው የሰንበቴ ገበያ የንግድ እና የግንኙነት ማዕከል ነው።
Discover

Tourism Areas

Experience the wonders of Jille — from ancient spiritual sites to vibrant markets.

አዋይቱ ፍል ውሃ

በፈውስ ባህሪያቱ እና ውብ በሆነው አካባቢው የሚታወቅ የተፈጥሮ ድንቅ።
Visit Site

የሰንበቴ ገበያ

በክልሉ ውስጥ በጣም ደማቅ እና ታሪካዊ ከሆኑት ገበያዎች አንዱ።
Visit Site

ጥሩሲና መስጊድ

የእምነት ምልክት እና የስነ-ህንፃ ውበት።
Visit Site

ፌቂ-አቡስ መስጊድ

ጥልቅ ታሪካዊ ጠቀሜታ ያለው ጥንታዊ መስጊድ።
Visit Site
Heritage

Cultural Values

The soul of Jille lives in its traditions, ceremonies, and communal bonds.

ሴራ አባ ኦርማ

ፍትህና ሰላምን የሚያረጋግጥ ባህላዊ አስተዳደር።

ባህላዊ ልብሶች

ማንነትን እና ጥበብን የሚያንፀባርቁ ደማቅ ልብሶች።

ባህላዊ ምግቦች

ለሥነ-ሥርዓቶች እና ለዕለት ተዕለት ኑሮ ልዩ ምግቦች።

ባህላዊ ጌጣጌጦች

በዝርዝር የተሰሩ እጅ-ጥበብ ጌጣጌጦች ሥነ-ሥርዓቶችን ያስጌጣሉ።

የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት

ቅዱስ እና ደስ ያለው ማህበረሰባዊ የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት።

የጋራ ርዳታ ባህል

በጂሌ ማህበረሰብ ውስጥ የጠነከረ የጋራ መረዳዳት ባህል።

ባህላዊ እርቅ

በሽማግሌዎች ሽምግልና የሚደረግ ጥንታዊ ግጭት መፍቻ።